በታይዋን የመሬት መንቀጥቀጥ

በታይዋን የመሬት መንቀጥቀጥ

February 7, 2018 1658 Like No Comments

አራት ህይወቶችን የቀጠፈው እንዲሁም ለ220ዎች ጉዳት ምክንያት የሆነው ከፍተኛ የታይዋን መሬት መንቀጥቀጥ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ይህ 6.4 ሬክተር ስኬል ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ እኩለ ሌሊት ሲሆን የደረሰው በከፍተኛ ሁኔታም በምስራቅ የምትገኘውን የባህር ዳርቻ ደሴቷን የሁሊየን ከተማ ተፅእኖ አድርሶባታል።

የሁሊየን ከተማ ነዋሪዎች ከፈራረሱ ቤቶቻቸው እንዲርቁ የተነገራቸው ሲሆን ይህንንም ተከትሎ 800 የሚሆኑ ነዋሪዎች በአካባቢው በሚገኙ ህንፃዎች ተጠልለዋል።

ሁሊየን ከአስር ሺ በላይ ነዋሪዎች ያሉባት ሲሆን በቱሪስት እምብርትነቷም ትታወቃለች።

ከከተማዋ የወጡ ምስሎች እንደሚያሳዩት በአውራ ጎዳናዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ህንፃዎች ፈራርሰዋል ከነዚህም ውስጥ ሆስፒታል እንደሚገኝበትም የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል።

“የመሬት መንቀጥቀጡ ሲፈጠር ሬስቶራችን ክፍት ነበር። ” በማለት በሆስፒታሉ አካባቢ የሬስቶራንት ባለቤት የሆነው ሊን ቺንግ ዌን ለሮይተርስ ተናግሯል።

“መሬት መንቀጥቀጡም ሲጀምር ሚስቴንና ልጆቼንም ይዠ ሰዎችን ለማዳን እየሮጥን ወጣን” ብሏል።

ወታደሮችን ጨምሮ የድንገተኛ አደገኛ ሰራተኞች ሰዎችን ለማዳን ሙሉ ሌሊት ሰርተዋል።

ምንም እንኳን 150 ሰዎችን ማዳን ቢችሉም በተከታታይ የመሬት መንቀጥቀጦቹ ባለመቋረጣቸው የማዳን ስራውን አክብዶታል።

የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ዛሬ ጥዋትም አምስት በፍርስራሹ ስር የተቀበሩ ሰዎችን ለማዳን በጥረት ላይ እንደነበሩም አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ከ140 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ የታይዋን ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል።

 

NEWS