የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለአፍሪካ ለማስተላለፍ

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለአፍሪካ ለማስተላለፍ

January 16, 2018 383 33 No Comments

አለም የሶፍትዌር ሰሪዎች እጥረት አለባት።በሌላ በኩል አፍሪካ ደግሞ በወጣት ህዝብ የተሞላች ነች።

አሜሪካና አውሮፓ አፍሪካዊ ሶፍትዌር ሰሪዎችን ቢያሰለጥኑ በዚህ የሰው ሃይል ይጠቀማሉ።

አንዲላ ሶፍትዌር ሰሪዎችን ናይጄሪያ ውስጥ አሰልጥኖ በአለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያስቀጥር ኩባንያ ነው።

በዚህ መልኩ አንዲላ እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት ያሰለጠናቸውን በማስቀጠር 40 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።

በ2016 ደግሞ ከፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ 24 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።በ2018 ደግሞ አንዲላ በግብፅም ማዕከል እንደሚከፍት ይጠበቃል።

በአፍሪካ ብዙ ሰዎች የባንክ ሂሳብ የላቸውም።በሌላ በኩል የሞባይል ክፍያ ስርአት ውጤታማ እንደሆነ ታይቷል።

በጥናት እንደታየው አፍሪካ መቶ ሚሊዮን ሰዎች የሞባይል የገንዘብ ሂሳብ የከፈቱባት አህጉር በመሆን አለምን ከሚመሩ ተርታ ተሰልፋለች።

በአሁኑ ወቅት የሞባይል የፋይናንስ አገልግሎት ብድርና ቁጠባን፣መድህንንና ሃዋላን ያካትታል።

ችግሩ በዚህ መልኩ የሚሰሩ ስርአቶች በርካታ መሆናቸውና አንድላይ አለመስራታቸው ነው።

ይህ ማለት ደግሞ አፍሪካ ውስጥ እቃዎችን በኢንተርኔት መግዛት አለመቻል ነው።

ለምሳሌ ፍለተርዌቭ የተባለው ስርአት በመላ አፍሪካ ለባንኮችና ለሌሎች ኩባንያዎችም የሞባይል ክፍያ ስርአት ዝርጋታን እውን አድርጓል።

በአውሮፓውያኑ 2017 የመጀበሪያው ሶስት ወር ውስጥ ፍለተርዌቭ 444 ሚሊዮን ዶላር በናይጄሪያ፣ጋናና ኬንያ አዘዋውሯል።

ከመጀበሪያው ጀምሮ ኩባንያው በአስር ሚሊዮን ዝውውሮች 1.2 ቢሊዮን ዶላር አስተላልፏል።

በዚያው ዓመት ኩባንያው ከአሜሪካ የአስር ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አግኝቷል።

ይህ ድጋፍ ለኩባንያው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት የሚጠበቅ ሲሆን በአፍሪካ ሰዎች በኢንተርኔት በቀላሉ የፈለጉትን መግዛት የሚችሉበትን ስርዓት እንደሚዘረጋ ይጠበቃል።

 

NEWS